37.Those drawn up in Ranks 1.The Opening 2.The Cow 3.The Family of Imraan 4.The Women 5.The Table 6.The Cattle 7.The Heights 8.The Spoils of War 9.The Repentance 10.Jonas 11.Hud 12.Joseph 13.The Thunder 14.Abraham 15.The Rock 16.The Bee 17.The Night Journey 18.The Cave 19.Mary 20.Taa-Haa 21.The Prophets 22.The Pilgrimage 23.The Believers 24.The Light 25.The Criterion 26.The Poets 27.The Ant 28.The Stories 29.The Spider 30.The Romans 31.Luqman 32.The Prostration 33.The Clans 34.Sheba 35.The Originator 36.Yaseen 37.Those drawn up in Ranks 38.The letter Saad 39.The Groups 40.The Forgiver 41.Explained in detail 42.Consultation 43.Ornaments of gold 44.The Smoke 45.Crouching 46.The Dunes 47.Muhammad 48.The Victory 49.The Inner Apartments 50.The letter Qaaf 51.The Winnowing Winds 52.The Mount 53.The Star 54.The Moon 55.The Beneficent 56.The Inevitable 57.The Iron 58.The Pleading Woman 59.The Exile 60.She that is to be examined 61.The Ranks 62.Friday 63.The Hypocrites 64.Mutual Disillusion 65.Divorce 66.The Prohibition 67.The Sovereignty 68.The Pen 69.The Reality 70.The Ascending Stairways 71.Noah 72.The Jinn 73.The Enshrouded One 74.The Cloaked One 75.The Resurrection 76.Man 77.The Emissaries 78.The Announcement 79.Those who drag forth 80.He frowned 81.The Overthrowing 82.The Cleaving 83.Defrauding 84.The Splitting Open 85.The Constellations 86.The Morning Star 87.The Most High 88.The Overwhelming 89.The Dawn 90.The City 91.The Sun 92.The Night 93.The Morning Hours 94.The Consolation 95.The Fig 96.The Clot 97.The Power, Fate 98.The Evidence 99.The Earthquake 100.The Chargers 101.The Calamity 102.Competition 103.The Declining Day, Epoch 104.The Traducer 105.The Elephant 106.Quraysh 107.Almsgiving 108.Abundance 109.The Disbelievers 110.Divine Support 111.The Palm Fibre 112.Sincerity 113.The Dawn 114.Mankind መሰለፍን በሚሰለፉት፡፡ መገሠጽንም በሚገሥጹት፤ ቁርኣንንም በሚያነቡት እምላለሁ፡፡ አምላካችሁ በእርግጥ አንድ ነው፡፡ የሰማያትና የምድር በመካከላቸው ያለውም ፍጡር ሁሉ ጌታ ነው፡፡ የምሥራቆችም ጌታ ነው፡፡ እኛ ቅርቢቱን ሰማይ በከዋክብት ጌጥ አጌጥናት፡፡ አመጸኛም ከሆነ ሰይጣን ሁሉ መጠበቅን ጠበቅናት፡፡ ወደላይኛው ሰራዊት አያዳምጡም፡፡ ከየወገኑም ሁሉ ችቦ ይጣልባቸዋል፡፡ የሚባረሩ ሲሆኑ (ይጣልባቸዋል)፡፡ ለእነሱም ዘውታሪ ቅጣት አላቸው፡፡ ንጥቂያን የነጠቀ ወዲያውም አብሪ ኮከብ የተከተለው ሲቀር፤ (እርሱ ይሰማዋል)፡፡ ጠይቃቸውም፤ እነርሱ በአፈጣጠር ይበልጥ የበረቱ ናቸውን? ወይስ እኛ (ከእነርሱ በፊት) የፈጠርነው? (ፍጡር) እኛ ከሚጣበቅ ጭቃ ፈጠርናቸው፡፡ ይልቁንም (በማስተባበላቸው) ተደነቅህ፤(ከመደነቅህ) ይሳለቃሉም፡፡ በተገሠጹም ጊዜ አይመለሱም፡፡ ተዓምርን ባዩም ጊዜ ለመሳለቅ ይጠራራሉ፡፡ ይላሉም «ይህ ግልጽ ድግምት እንጂ ሌላ አይደለም፡፡ «በሞትንና ዐፈርና አጥንቶችም በኾን ጊዜ እኛ የምንቀሰቀስ ነን «የቀድሞዎቹ አባቶችንም? (ይላሉ)፡፡ «አዎን እናንተ ወራዶች ሆናችሁ (ትነሳላችሁ)» በላቸው፡፡ እርሷም አንዲት ጩኸት ብቻ ናት፡፡ እነርሱም ወዲያውኑ (ምን እንደሚፈጸምባቸው) ያያሉ፡፡ «ዋ ጥፋታችን! ይህ የፍርዱ ቀን ነው» ይላሉም፡፡ «ይህ ያ በእርሱ ታስተባብሉ የነበራችሁት መለያው ቀን ነው» (ይባላሉ)፡፡ (ለመላእክቶችም) «እነዚያን ነፍሶቻቸውን የበደሉትን ሰዎች ጓደኞቻቸውንም ይግገዟቸው የነበሩትንም (ጣዖታት) ሰብስቡ፡፡ «ከአላህ ሌላ (የሚገዙዋቸውን ሰብስቧቸው) ወደ እሳት መንገድም ምሩዋቸው፡፡ «አቁሟቸውም፡፡ እነርሱ ተጠያቂዎች ናቸውና» (ይባላል)፡፡ (ለእነርሱም) «የማትረዳዱት ለእናንተ ምን አላችሁ? (ይባላሉ)፡፡ በእርግጥ እነርሱ ዛሬ እጃቸውን የሰጡ ወራዳዎች ናቸው፡፡ የሚወቃቀሱም ሆነው ከፊላቸው በከፊሉ ላይ ይመጣሉ፡፡ (ለአስከታዮቹ) እናንተ ከስተቀኝ ትመጡብን ነበር ይላሉ፡፡ (አስከታዮቹም) ይላሉ «አይደለም ፈጽሞ ምእምናን አልነበራችሁም፡፡ «ለእኛም በእናንተ ላይ ምንም ስልጣን አልነበረንም፡፡ በእርግጥ እናንተ ጠማሞች ሕዝቦች ነበራችሁ፡፡ «በእኛም ላይ የጌታችን ቃል ተረጋገጠብን፤ እኛ (ሁላችንም ቅጣቱን) ቀማሾች ነን፡፡ «ወደ ጥምመት ጠራናችሁም፡፡ እኛ ጠማሞች ነበርንና» (ይላሉ)፡፡ ስለዚህ እነርሱ በዚያ ቀን በቅጣቱ ነጋሪዎች ናቸው፡፡ እኛ በአመጸኞች ሁሉ እንደዚሁ እንሠራለን፡፡ እነርሱ ከአላህ ሌላ አምላክ የለም በተባሉ ጊዜ ይኮሩ ነበሩ፡፡ እኛ ለዕብድ ባለቅኔ ብለን አማልክቶቻችንን የምንተው ነን? ይሉም ነበር፡፡ አይደለም እውነቱን (ሃይማኖት) አመጣ፡፡ መልክተኞቹንም እውነተኛነታቸውን አረጋገጠ፡፡ እናንተ አሳማሚውን ቅጣት በእርግጥ ቀማሾች ናችሁ፡፡ ትሠሩትም የነበራችሁትን እንጂ ሌላን አትመነዱም፡፡ ግን ምርጥ የሆኑት የአላህ ባሮች (ቅጣትን አይቀምሱም)፡፡ እነዚያ ለእነርሱ የታወቀ ሲሳይ አላቸው፡፡ ፍራፍሬዎች (አሏቸው) እነርሱም የተከበሩ ናቸው፤ በድሎት ገነቶች ውስጥ፡፡ ፊት ለፊት የሚታያዩ ሲሆኑ በአልጋዎች ላይ (ይንፈላሰሳሉ)፡፡ ከሚመነጭ ወይን ጠጅ በያዘ ብርጭቆ በእነርሱ ላይ ይዞርባቸዋል፡፡ ነጭ ለጠጪዎች ጣፋጭ ከኾነች፡፡ በእርሷ ውስጥም ምታት የለባትም፡፡ እነርሱም ከእርሷ የሚሰክሩ አይደሉም፡፡ እነርሱም ዘንድ ዓይናቸውን (በባሎቻቸው ላይ) አሳጣሪዎች የኾኑ ዓይናማዎች አልሉ፡፡ እነርሱ ልክ የተሸፈነ (የሰጎን) ዕንቁላል ይመስላሉ፡፡ የሚጠያየቁም ሆነው ከፊላቸው ወደ ከፊሉ ይመጣሉ፡፡ ከእነርሱ የሆነ ተናጋሪ ይላል «እኔ ጓደኛ ነበረኝ፡፡ «በእርግጥ አንተ ከሚያምኑት ነህን? የሚል፡፡ «በሞትንና ዐፈር አጥንቶችም በሆን ጊዜ እኛ በእርግጥ እንመረመራለን?» (የሚል)፡፡ እናንተ ተመልካቾች ናችሁን? ይላል፡፡ ይመለከታልም፤ በገሀነም መካከልም (ጓደኛውን) ያየዋል፡፡ ይላል «በአላህ እምላለሁ፤ በእርግጥ ልታጠፋኝ ቀርበህ ነበር፡፡ «የጌታየም ጸጋ ባልነበረ ኖሮ ወደ እሳት ከሚቀርቡት እሆን ነበር፡፡» (የገነት ሰዎች ይላሉ) «እኛ የምንሞት አይደለንምን «የመጀመሪያይቱ መሞታችን ብቻ ስትቀር፡፡ እኛም የምንቅቀጣ አይደለንምን?» (ይላሉ)፡፡ ይህ (ለገነት ሰዎች የተወሳው) እርሱ በእርግጥ ታላቅ ዕድል ነው፡፡ ለዚህ ብጤ ሠሪዎች ይሥሩ፡፡ በመስተንግዶነት ይህ ይበልጣልን? ወይስ የዘቁም ዛፍ እኛ ለበዳዮች ፈተና አድርገናታል፡፡ እርሷ በገሀነም አዘቅት ውስጥ የምትወጣ ዛፍ ናት፡፡ እንቡጧ ልክ የሰይጣናት ራሶች ይመስላል፡፡ እነርሱም ከእርሷ በይዎች ናቸው፤ ሆዶችንም ከእርሷ ሞይዎች ናቸው፡፡ ከዚያም ለእነርሱ በእርሷ ላይ ከተኳሳ ውሃ ቅልቅል (መጠጥ) አልላቸው፡፡ ከዚያም መመለሻቸው ወደ ተጋጋመች እሳት ነው፡፡ እነሱ አባቶቻቸውን የተሳሳቱ ሆነው አግኝተዋልና፡፡ እነሱም በፈለጎቻቸው ላይ ይገሰግሳሉና፡፡ ከእነርሱ በፊትም የቀድሞዎቹ (ሕዝቦች) አብዛኞቻቸው በእርግጥ ተሳስተዋል፡፡ በውስጣቸውም አስፈራሪዎችን በእርግጥ ልከናል፡፡ የተስፈራሪዎቹም መጨረሻ እንዴት እንደነበረ ተመልከት፡፡ ምርጥ የሆኑት የአላህ ባሮች ብቻ ሲቀሩ፡፡ ኑሕም በእርግጥ ጠራን፡፡ ጥሪውን ተቀባዮቹም ምንኛ አማርን እርሱንም ቤተሰቦቹንም ከከባድ ጭንቅ አዳንን፡፡ ዘሮቹንም እነርሱን ብቻ ቀሪዎች አደረግን፤ በርሱም ላይ በኋለኞቹ ሕዝቦች ውስጥ (መልካም ዝናን) ተውን፡፡ «በዓለማት ውስጥ ሰላም በኑሕ ላይ ይኹን፡፡» እኛ እንደዚሁ መልካም ሠሪዎችን እንመነዳለን፡፡ እርሱ ከምእምናን ባሮቻችን ነውና፡፡ ከዚያም ሌሎቹን አሰጠምን፡፡ ኢብራሂምም በእርግጥ ከተከታዮቹ ነው፡፡ ወደ ጌታው በቅን ልብ በመጣ ጊዜ (የኾነውን አስታውስ)፡፡፡ «ለአባቱና ለሕዝቦቹ ምንን ትግገዛላችሁ?» ባለ ጊዜ፡፡ «ለቅጥፈት ብላችሁ ከአላህ ሌላ አማልክትን ትሻላችሁን «በዓለማትም ጌታ ሃሳባችሁ ምንድን ነው?» አለ፡፡ በከዋክብትም መመልከትን ተመለከተ፡፡ «እኔ በሽተኛ ነኝም» አለ፡፡ ከእርሱም የሸሹ ሆነው ኼዱ፡፡ ወደ አማልክቶቻቸውም ተዘነበለ፡፡ አለም፡- «አትበሉምን?» «የማትናገሩት ለናንተ ምን አላችሁ?» በኀይል የሚመታቸውም ሆኖ በእነርሱ ላይ በድብቅ ተዘነበለ፡፡ ወደእርሱም (ሰዎቹ) እየሮጡ መጡ፡፡ አላቸው «የምትጠርቡትን ትግገዛላችሁን?» «አላህ እናንተንም የምትሠሩትንም የፈጠረ ሲኾን፡፡» «ለእርሱም ግንብን ገንቡ በእሳት ነበልባል ውስጥ ጣሉትም» አሉ፡፡ በእርሱም ተንኮልን አሰቡ፡፡ ዝቅተኞችም አደረግናቸው፡፡ አለም «እኔ ወደ ጌታዬ ኼያጅ ነኝ፡፡ በእርግጥ ይመራኛልና፡፡» ጌታዬ ሆይ! ከመልካሞቹ የሆነን (ልጅ) ስጠኝ፡፡ ታጋሽ በሆነ ወጣት ልጅም አበሰርነው፡፡ ከእርሱ ጋርም ለሥራ በደረሰ ጊዜ «ልጄ ሆይ! እኔ በሕልሜ እኔ የማርድህ ሆኜ አያለሁ፡፡ ተመልከትም፤ ምን ታያለህ?» አለው፡፡ «አባቴ ሆይ! የታዘዝከውን ሥራ፡፡ አላህ ቢሻ ከታጋሾቹ ሆኜ ታገኘኛለህ» አለ፡፡ ሁለቱም ትዕዛዙን በተቀበሉና በግንባሩም ጎን ላይ በጣለው ጊዜ (የሆነው ሆነ)፡፡ ጠራነውም፤ (አልነው) «ኢብራሂም ሆይ ራእይቱን በእውነት አረጋገጥክ፡፡» እኛ እንደዚሁ መልካም ሠሪዎችን እንመነዳለን፡፡ ይህ እርሱ በእውነት ግልጽ ፈተና ነው፡፡ በታላቅ ዕርድም (መስዋዕት) ተቤዠነው፡፡ በእርሱም ላይ በኋለኞቹ ሕዝቦች ውስጥ መልካም ዝናን አስቀረንለት፡፡ ሰላም በኢብራሂም ላይ ይሁን፡፡ እንደዚሁ መልካም ሠሪዎችን ሁሉ እንመነዳለን፡፡ እርሱ በእርግጥ ካመኑት ባሮቻችን ነው፡፡ በኢስሐቅም አበሰርነው፡፡ ከመልካሞቹ የሆነ ነቢይ ሲሆን፡፡ በእርሱና በኢስሐቅ ላይም ባረክን፡፡ ከሁለቱም ዘሮች በጎ ሠሪ አልለ፡፡ ለነፍሱ ግልጽ በዳይም አለ፡፡ በሙሳና በሃሩን ላይም በእርግጥ ለገስን፡፡ እነርሱንም ሕዝቦቻቸውንም ከታላቅ ጭንቅ አዳንን፡፡ ረዳናቸውም፡፡ እነርሱም አሸናፊዎች ነበሩ፡፡ በጣም የተብራራውንም መጽሐፍ ሰጠናቸው፡፡ ቀጥተኛውንም መንገድ መራናቸው፡፡ በሁለቱም ላይ በኋለኞቹ ሕዝቦች ውስጥ መልካም ዝናን ተውንላቸው፡፡ ሰላም በሙሳና በሃሩን ላይ ይሁን፡፡ እኛ እንደዚሁ በጎ አድራጊዎችን ሁሉ እንመነዳለን፡፡ ሁለቱም በእርግጥ ከአመኑት ባሮቻችን ናቸው፡፡ ኢልያስም በእርግጥ ከመልክተኞቹ ነው፡፡ ለሕዝቦቹ ባለ ጊዜ (አስታውስ)፤ አላህን አትፈሩምን በዕልን ትገዛላችሁን? ከሰዓሊዎቹ ሁሉ ይበልጥ በጣም አሳማሪ የሆነውንም አምላክ ትተዋላችሁን አላህን ጌታችሁንና የቀድሞዎቹ አባቶቻችሁን ጌታ (ትተዋላችሁን) አስተባበሉትም፡፡ ስለዚህ እነርሱ (ለቅጣት) የሚጣዱ ናቸው፡፡ ንጹሕ የተደረጉት የአላህ ባሮች ብቻ ሲቀሩ፡፡ በእርሱ ላይም በኋለኞቹ ሕዝቦች ውስጥ መልካም ዝናን ተውንለት፡፡ ሰላም በኢልያሲን ላይ ይሁን፡፡ እኛ እንደዚሁ መልካም ሠሪዎችን እንመነዳለን፡፡ እርሱ በእርግጥ ከምእመናን ባሮቻችን ነው፡፡ ሉጥም በእርግጥ ከመልክተኞቹ ነው፡፡ እርሱንና ቤተሰቦቹን ሁሉንም በአዳንናቸው ጊዜ (አስታውስ)፡፡ (በቅጣቱ ውስጥ) ከቀሪዎቹ የሆነችው አሮጊት ብቻ ስትቀር፡፡ ከዚያም ሌሎቹን አጠፋን፡፡ እናንተም ያነጋችሁ ስትሆኑ በእነርሱ (መኖሪያዎች) ላይ (በቀን) ታልፋላችሁ፡፡ በሌሊትም (ታልፋላችሁ)፤ ልብም አታደርጉምን ዩኑስም በእርግጥ ከመልክተኞቹ ነው፡፡ ወደ ተመላው መርከብ በኮበለለ ጊዜ (አስታውስ)፡፡ ዕጣም ተጣጣለ፡፡ ከተሸነፉትም ሆነ፡፡ እርሱም ተወቃሽ ሲሆን ዐሳው ዋጠው፡፡ እርሱ ለጌታው ከአወዳሾቹ ባልሆነም ኖሮ፤ እስከሚቀሰቀሱበት ቀን ድረስ በሆዱ ውስጥ በቆየ ነበር፡፡ እርሱ በሽተኛ ሆኖ በቃይ በሌለው (በባሕር) ዳርቻ ላይ ጣልነውም፡፡ በእርሱም ላይ (በአጠገቡ) ከቅል የሆነችን ዛፍ አበቀልን፡፡ ወደ መቶ ሺሕ ሰዎችም (ዳግመኛ) ላክነው፡፡ ከቶውንም ይጨምራሉ፡፡ አመኑም፡፡ እስከ ጊዜ ድረስም አጣቀምናቸው፡፡ (የመካን ሰዎች) ጠይቃቸውም፡፡ «ለጌታህ ሴቶች ልጆች ለእነርሱም ወንዶች ልጆች ይኖራልን?» ወይስ እኛ እነርሱ የተጣዱ ሆነው መላእክትን ሴቶች አድርገን ፈጠርን ንቁ! እነርሱ ከቅጥፈታቸው (የተነሳ) ይላሉ፡ «አላህ (መላእክትን) ወለደ፡፡» እነርሱም በእርግጥ ውሸታሞች ናቸው፡፡ በወንዶች ልጆች ላይ ይልቅ ሴቶችን ልጆች መረጥን ለእናንተ ምን (አስረጅ) አላችሁ? እንዴት ትፈርዳላችሁ አትገነዘቡምን ወይስ ለእናንተ ግልጽ አስረጅ አላችሁን «እውነተኞች እንደ ሆናችሁ መጽሐፋችሁን አምጡ» (በላቸው)፡፡ በአላህና በአጋንንት መካከልም ዝምድናን አደረጉ፡፡ አጋንንትም እነርሱ (ይህን ባዮች በእሳት) የሚጣዱ መሆናቸውን በእርግጥ ዐውቀዋል፡፡ አላህ ከሚመጥኑት ሁሉ ጠራ፡፡ ግን የተመረጡት የአላህ ባሮች (በአላህ ላይ አይዋሹም)፡፡ እናንተም የምትገዟቸውም ሁሉ፤ በእርሱ (በአላህ) ላይ አንድንም አጥማሚዎች አይደላችሁም፡፡ ያንን እርሱ ገሀነምን ገቢ የሆነውን ሰው ቢሆን እንጅ፡፡ (ጂብሪል አለ) ከእኛም አንድም የለም፤ ለእርሱ የታወቀ ደረጃ ያለው ቢሆን እንጅ፡፡ እኛም (ጌታን ለመግገዛት) ተሰላፊዎቹ እኛ ነን፡፡ እኛም (አላህን) አጥሪዎቹ እኛ ነን፡፡ እነርሱም (ከሓዲዎቹ) በእርግጥ ይሉ ነበሩ፡ «ከቀድሞዎቹ (መጻሕፍት) ገሳጭ መጽሐፍ እኛ ዘንድ በነበረን ኖሮ፤ «የአላህ ምርጦች ባሮች በሆን ነበር፡፡» ግን (ቁርኣኑ በመጣላቸው ጊዜ) በእርሱ ካዱ፡፡ ወደፊትም በእርግጥ ያውቃሉ፡፡ (የእርዳታ) ቃላችንም መልክተኞች ለሆኑት ባሮቻችን በእውነት አልፋለች፡፡ እነርሱ ተረጂዎቹ እነርሱ ናቸው፡፡ ሰራዊቶቻችንም በእርግጥ አሸናፊዎቹ እነርሱ ናቸው፡፡ ከእነርሱም (ከመካ ከሓዲዎች) እስከ ጥቂት ጊዜ ድረስ ዙር (ተዋቸው)፡፡ እያቸውም ወደፊትም (የሚደርስባቸውን) ያያሉ፡፡ በቅጣታችንም ያቻኩላሉን በቀያቸውም በወረደ ጊዜ የተስፈራሪዎቹ ንጋት ከፋ እነርሱንም እስከ (ጥቂት) ጊዜ ድረስ ተዋቸው፡፡ ተመልከትም በእርግጥም ያያሉ፡፡ የማሸነፍ ጌታ የሆነው ጌታህ ከሚሉት ሁሉ ጠራ፡፡ በመልክተኞቹም ላይ ሰላም ይኹኑ፤ ምስጋናም ለዓለማት ጌታ ለአላህ ይሁን፡፡ Prev Next 1.The Opening 2.The Cow 3.The Family of Imraan 4.The Women 5.The Table 6.The Cattle 7.The Heights 8.The Spoils of War 9.The Repentance 10.Jonas 11.Hud 12.Joseph 13.The Thunder 14.Abraham 15.The Rock 16.The Bee 17.The Night Journey 18.The Cave 19.Mary 20.Taa-Haa 21.The Prophets 22.The Pilgrimage 23.The Believers 24.The Light 25.The Criterion 26.The Poets 27.The Ant 28.The Stories 29.The Spider 30.The Romans 31.Luqman 32.The Prostration 33.The Clans 34.Sheba 35.The Originator 36.Yaseen 37.Those drawn up in Ranks 38.The letter Saad 39.The Groups 40.The Forgiver 41.Explained in detail 42.Consultation 43.Ornaments of gold 44.The Smoke 45.Crouching 46.The Dunes 47.Muhammad 48.The Victory 49.The Inner Apartments 50.The letter Qaaf 51.The Winnowing Winds 52.The Mount 53.The Star 54.The Moon 55.The Beneficent 56.The Inevitable 57.The Iron 58.The Pleading Woman 59.The Exile 60.She that is to be examined 61.The Ranks 62.Friday 63.The Hypocrites 64.Mutual Disillusion 65.Divorce 66.The Prohibition 67.The Sovereignty 68.The Pen 69.The Reality 70.The Ascending Stairways 71.Noah 72.The Jinn 73.The Enshrouded One 74.The Cloaked One 75.The Resurrection 76.Man 77.The Emissaries 78.The Announcement 79.Those who drag forth 80.He frowned 81.The Overthrowing 82.The Cleaving 83.Defrauding 84.The Splitting Open 85.The Constellations 86.The Morning Star 87.The Most High 88.The Overwhelming 89.The Dawn 90.The City 91.The Sun 92.The Night 93.The Morning Hours 94.The Consolation 95.The Fig 96.The Clot 97.The Power, Fate 98.The Evidence 99.The Earthquake 100.The Chargers 101.The Calamity 102.Competition 103.The Declining Day, Epoch 104.The Traducer 105.The Elephant 106.Quraysh 107.Almsgiving 108.Abundance 109.The Disbelievers 110.Divine Support 111.The Palm Fibre 112.Sincerity 113.The Dawn 114.Mankind