31.Luqman 1.The Opening 2.The Cow 3.The Family of Imraan 4.The Women 5.The Table 6.The Cattle 7.The Heights 8.The Spoils of War 9.The Repentance 10.Jonas 11.Hud 12.Joseph 13.The Thunder 14.Abraham 15.The Rock 16.The Bee 17.The Night Journey 18.The Cave 19.Mary 20.Taa-Haa 21.The Prophets 22.The Pilgrimage 23.The Believers 24.The Light 25.The Criterion 26.The Poets 27.The Ant 28.The Stories 29.The Spider 30.The Romans 31.Luqman 32.The Prostration 33.The Clans 34.Sheba 35.The Originator 36.Yaseen 37.Those drawn up in Ranks 38.The letter Saad 39.The Groups 40.The Forgiver 41.Explained in detail 42.Consultation 43.Ornaments of gold 44.The Smoke 45.Crouching 46.The Dunes 47.Muhammad 48.The Victory 49.The Inner Apartments 50.The letter Qaaf 51.The Winnowing Winds 52.The Mount 53.The Star 54.The Moon 55.The Beneficent 56.The Inevitable 57.The Iron 58.The Pleading Woman 59.The Exile 60.She that is to be examined 61.The Ranks 62.Friday 63.The Hypocrites 64.Mutual Disillusion 65.Divorce 66.The Prohibition 67.The Sovereignty 68.The Pen 69.The Reality 70.The Ascending Stairways 71.Noah 72.The Jinn 73.The Enshrouded One 74.The Cloaked One 75.The Resurrection 76.Man 77.The Emissaries 78.The Announcement 79.Those who drag forth 80.He frowned 81.The Overthrowing 82.The Cleaving 83.Defrauding 84.The Splitting Open 85.The Constellations 86.The Morning Star 87.The Most High 88.The Overwhelming 89.The Dawn 90.The City 91.The Sun 92.The Night 93.The Morning Hours 94.The Consolation 95.The Fig 96.The Clot 97.The Power, Fate 98.The Evidence 99.The Earthquake 100.The Chargers 101.The Calamity 102.Competition 103.The Declining Day, Epoch 104.The Traducer 105.The Elephant 106.Quraysh 107.Almsgiving 108.Abundance 109.The Disbelievers 110.Divine Support 111.The Palm Fibre 112.Sincerity 113.The Dawn 114.Mankind አ.ለ.መ. (አሊፍ ላም ሚም)፡፡ ይህች ጥበብ ከተመላው መጽሐፍ አንቀጾች ናት፡፡ ለበጎ አድራጊዎች መሪና እዝነት ስትኾን፡፡ ለእነዚያ ሶላትን አስተካክለው ለሚያደርሱት፣ ዘካንም ለሚሰጡት፣ እነርሱም በመጨረሻይቱ ዓለም እነርሱ የሚያረጋግጡ ለሆኑት፡፡ እነዚያ ከጌታቸው በሆነ ቅን መንገድ ላይ ናቸው፡፡ እነዚያም እነርሱ ምኞታቸውን ያገኙ ናቸው፡፡ ከሰዎችም ያለ ዕውቀት ሆኖ ከአላህ መንገድ ሊያሳስትና ማላገጫ አድርጎ ሊይዛት አታላይ ወሬን የሚገዛ አልለ፡፡ እነዚያ ለእነርሱ አዋራጅ ቅጣት አላቸው፡፡ አንቀጾቻችንም በእርሱ ላይ በሚነበቡ ጊዜ እንዳልሰማትና በጆሮቹ ድንቁርና እንዳለበት የኮራ ሆኖ ይዞራል፡፡ በአሳማሚ ቅጣትም አብስረው፡፡ እነዚያ ያመኑና መልካሞችንም የሠሩ ለእነርሱ የጸጋ ገነቶች አሏቸው፡፡ በእርሷ ውስጥ ዘውታሪዎች ሲሆኑ፤ አላህም እውነተኛን ተስፋ ቃል ገባላቸው፡፡ እርሱም አሸናፊው ጥበበኛው ነው፡፡ ሰማያትን ያለምታዩዋት አዕማድ (ምሰሶዎች) ፈጠረ፡፡ በምድርም ውስጥ በእናንተ እንዳታረገርግ ተራራዎችን ጣለ፡፡ በእርሷም ላይ ከተንቀሳቃሽ ሁሉ በተነ፡፡ ከሰማይም ውሃን አወረድን፡፡ በእርሷም ውስጥ ከመልካም ዓይነት ሁሉ አበቀልን፡፡ ይህ የአላህ ፍጡር ነው፡፡ እነዚያ ከእርሱ ሌላ ያሉት ምንን እንደፈጠሩ እስኪ አሳዩኝ፡፡ በእውነቱ በዳዮቹ በግልጽ ጥመት ውስጥ ናቸው፡፡ ለሉቅማንም ጥበብን በእርግጥ ሰጠነው፡፡ (አልነውም)፡- «አላህን አመስግን፡፡» ያመሰገነም ሰው የሚያመሰግነው ለራሱ ብቻ ነው፡፡ የካደም ሰው (በራሱ ላይ ነው)፡፡ አላህ ተብቃቂ ምስጉን ነውና፡፡ ሉቅማንም ለልጁ እርሱ የሚገሥጸው ሲኾን «ልጄ ሆይ! በአላህ (ጣዖትን) አታጋራ፡፡ ማጋራት ታላቅ በደል ነውና» ያለውን (አስታውስ)፡፡ ሰውንም በወላጆቹ (በጎ እንዲያደርግ) በጥብቅ አዘዝነው፡፡ እናቱ ከድካም በላይ በሆነ ድካም አረገዘችው፡፡ ጡት መጣያውም በሁለት ዓመት ውስጥ ነው፡፡ ለእኔም ለወላጆችህም አመስግን በማለት (አዘዝነው)፡፡ መመለሻው ወደኔ ነው፡፡ ለአንተ በእርሱ ዕውቀት የሌለህን ነገር በእኔ እንድታጋራ ቢታገሉህም አትታዘዛቸው፡፡ በቅርቢቱም ዓለም፤ በመልካም ሥራ ተወዳጃቸው፡፡ ወደእኔም የተመለሰን ሰው መንገድ ተከተል፡፡ ከዚያም መመለሻችሁ ወደእኔ ነው፡፡ ትሠሩት የነበራችሁትንም ሁሉ እነግራችኋለሁ፤ (አልነው)፡፡ (ሉቅማንም አለ) «ልጄ ሆይ! እርሷ የሰናፍጭ ቅንጣት ክብደት ያህል ብትሆንና በቋጥኝ ውስጥ ወይም በሰማያት ውስጥ ወይም በምድር ውስጥ ብትሆን አላህ ያመጣታል፡፡ አላህ ሩኅሩኅ ውስጥ ዐዋቂ ነውና፡፡ «ልጄ ሆይ! ሶላትን አስተካክለህ ስገድ፡፡ በበጎ ነገርም እዘዝ፡፡ ከሚጠላም ሁሉ ከልክል፡፡ በሚያገኝህም መከራ ላይ ታገስ፡፡ ይህ በምር ከሚያዙ ነገሮች ነው፡፡ «ጉንጭህንም (በኩራት) ከሰዎች አታዙር፡፡ በምድርም ላይ ተንበጥርረህ አትሂድ፡፡ አላህ ተንበጥራሪን ጉረኛን ሁሉ አይወድምና፡፡ «በአካኼድህም መካከለኛ ኹን፡፡ ከድምጽህም ዝቅ አድርግ፡፡ ከድምጾች ሁሉ አስከፊው የአህዮች ድምጽ ነውና፡፡» አላህ በሰማያት ያለውንና በምድርም ያለውን ሁሉ ለእናንተ ያገራላችሁ ጸጋዎቹንም ግልጽም ድብቅም ሲኾኑ የሞላላችሁ መኾኑን አታዩምን? ከሰዎችም ያለ ዕውቀትና ያለ መሪ፣ ያለግልጽ መጽሐፍም በአላህ የሚከራከር አልለ፡፡ ለእነርሱም አላህ ያወረደውን ተከተሉ በተባሉ ጊዜ አይደለም በእርሱ ላይ አባቶቻችንን ያገኘንበትን እንከተላለን ይላሉ፡፡ ሰይጣን ወደ እሳት ቅጣት የሚጠራቸው ቢሆንም (ይከተሉዋቸዋልን) እርሱ መልካም ሠሪ ሆኖ ፊቱን ወደ አላህ የሚሰጥም ሰው ጠንካራን ገመድ በእርግጥ ጨበጠ፡፡ የነገሩም ሁሉ ፍጻሜ ወደ አላህ ነው፡፡ የካደም ሰው ክህደቱ አያሳዝንህ፡፡ መመለሻቸው ወደኛ ነው፤ የሠሩትንም ሁሉ እንነግራቸዋለን፡፡ አላህ በልቦች ውስጥ ያለን ሁሉ ያውቃልና፡፡ ጥቂትን እናጣቅማቸዋለን፡፡ ከዚያም ወደ ብርቱ ቅጣት እናስገድዳቸዋለን፡፡ ሰማያትንና ምድርንም የፈጠረ ማን እንደሆነ ብትጠይቃቸው በእርግጥ አላህ ነው ይላሉ፡፡ ምስጋና ለአላህ ይገባው በላቸው፡፡ ይልቁንም አብዛኛዎቹ አያውቁም፡፡ በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የአላህ ነው፡፡ አላህ እርሱ ተብቃቂ ምስጉን ነው፡፡ ከዛፍም በምድር ያለው ሁሉ ብእሮች ቢሆኑ ኖሮ ባሕሩም ከእርሱ (ማለቅ) በኋላ ሰባት ባህሮች የሚጨመሩለት ሆኖ (ቀለም ቢሆንና ቢጻፍባቸው) የአላህ ቃላት ባላለቀች ነበር፡፡ አላህ አሸናፊ ጥበበኛ ነውና፡፡ እናንተን መፍጠርና እናንተን መቀስቀስ እንደ አንዲት ነፍስ እንጂ ሌላ አይደለም፡፡ አላህ ሰሚ ተመልካች ነውና፡፡ አላህ ሌሊትን በቀን ውስጥ የሚያስገባ፣ ቀንንም በሌሊት ውስጥ የሚያስገባ፣ ፀሐይንና ጨረቃንም የገራ መሆኑን አታይምን? ሁሉም እስከ ተወሰነ ጊዜ ድረስ ይሮጣሉ፡፡ አላህም በምትሠሩት ሁሉ ውስጠ ዐዋቂ ነው፡፡ ይህ አላህ እርሱ እውነት ከእርሱም ሌላ የሚግገዙት (ጣዖት) ውሸት በመሆኑና አላህም እርሱ የበላይ ታላቅ በመሆኑ ነው፡፡ ከአስደናቂ ምልክቶቹ ሊያሳያችሁ መርከቦች በአላህ ችሮታ በባህር ውስጥ የሚንሻለሉ መሆናቸውን አታይምን? በዚህ ውስጥ በጣም ታጋሽ አመስጋኝ ለሆኑ ሁሉ ተዓምራቶች አሉበት፡፡ እንደ ጥላዎችም የሆነ ማዕበል በሸፈናቸው ጊዜ አላህን ሃይማኖትን ለእርሱ ብቻ ያጠሩ ሆነው ይጠሩታል፡፡ ወደ የብስም ባዳናቸው ጊዜ ከእነሱ ትክክለኛም አልለ፡፡ (ከእነርሱም የሚክድ አለ)፡፡ በአንቀጾቻችንም አታላይ ከዳተኛ ሁሉ እንጂ ሌላው አይክድም፡፡ እናንተ ሰዎች ሆይ! ጌታችሁን ፍሩ፡፡ ወላጅም ከልጁ (በምንም) የማይጠቅምበትን፤ ተወላጅም እርሱ ወላጅን በምንም ጠቃሚ የማይሆንበትን ቀን ፍሩ፡፡ የአላህ ቀጠሮ እውነት ነውና፡፡ ቅርቢቱም ሕይወት አትሸንግላችሁ፡፡ በአላህም (መታገስ) አታላዩ (ሰይጣን) አያታልላችሁ፡፡ አላህ የሰዓቲቱ ዕውቀት እርሱ ዘንድ ብቻ ነው፡፡ ዝናብንም ያወርዳል፡፡ በማሕፀኖችም ውስጥ ያለን ሁሉ ያውቃል፡፡ ማንኛይቱ ነፍስም ነገ የምትሠራውን አታውቅም፡፡ ማንኛይቱ ነፍስም በየትኛው ምድር እንደምትሞት አታውቅም፡፡ አላህ ዐዋቂ ውስጠ ዐዋቂ ነው፡፡ Prev Next 1.The Opening 2.The Cow 3.The Family of Imraan 4.The Women 5.The Table 6.The Cattle 7.The Heights 8.The Spoils of War 9.The Repentance 10.Jonas 11.Hud 12.Joseph 13.The Thunder 14.Abraham 15.The Rock 16.The Bee 17.The Night Journey 18.The Cave 19.Mary 20.Taa-Haa 21.The Prophets 22.The Pilgrimage 23.The Believers 24.The Light 25.The Criterion 26.The Poets 27.The Ant 28.The Stories 29.The Spider 30.The Romans 31.Luqman 32.The Prostration 33.The Clans 34.Sheba 35.The Originator 36.Yaseen 37.Those drawn up in Ranks 38.The letter Saad 39.The Groups 40.The Forgiver 41.Explained in detail 42.Consultation 43.Ornaments of gold 44.The Smoke 45.Crouching 46.The Dunes 47.Muhammad 48.The Victory 49.The Inner Apartments 50.The letter Qaaf 51.The Winnowing Winds 52.The Mount 53.The Star 54.The Moon 55.The Beneficent 56.The Inevitable 57.The Iron 58.The Pleading Woman 59.The Exile 60.She that is to be examined 61.The Ranks 62.Friday 63.The Hypocrites 64.Mutual Disillusion 65.Divorce 66.The Prohibition 67.The Sovereignty 68.The Pen 69.The Reality 70.The Ascending Stairways 71.Noah 72.The Jinn 73.The Enshrouded One 74.The Cloaked One 75.The Resurrection 76.Man 77.The Emissaries 78.The Announcement 79.Those who drag forth 80.He frowned 81.The Overthrowing 82.The Cleaving 83.Defrauding 84.The Splitting Open 85.The Constellations 86.The Morning Star 87.The Most High 88.The Overwhelming 89.The Dawn 90.The City 91.The Sun 92.The Night 93.The Morning Hours 94.The Consolation 95.The Fig 96.The Clot 97.The Power, Fate 98.The Evidence 99.The Earthquake 100.The Chargers 101.The Calamity 102.Competition 103.The Declining Day, Epoch 104.The Traducer 105.The Elephant 106.Quraysh 107.Almsgiving 108.Abundance 109.The Disbelievers 110.Divine Support 111.The Palm Fibre 112.Sincerity 113.The Dawn 114.Mankind