110.Divine Support

  1. የአላህ እርዳታና (መካን) መክፈት በመጣ ጊዜ፤
  2. ሰዎችንም ጭፍሮች እየኾኑ፤ በአላህ ሃይማኖት ውስጥ ሲገቡ ባየህ ጊዜ፤
  3. ጌታህን ከማመስገን ጋር አጥራው፡፡ ምሕረትንም ለምነው፡፡ እርሱ ጸጸትን በጣም ተቀባይ ነውና፡፡